ከሱፐርኢንቴንደንቱ የተጻፈ ደብዳቤ

ክቡራን የኤሲፒኤስ ቤተሰቦች፣

ለ2021-2022 የትምህርት ዘመን የፊት ለፊት የክፍል ውስጥ እና የኦንላይ ኮርስዋች ወደ 400 የሚጠጉ የትምህርት መስኮች ከስድስተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ላሉ ተማሪዋች ስናቀርብ በደስታ ነው። በኤሲፒኤስ በርካታ የዳበሩ እና የተለያዪ ኮርሶች አሉ እና እነዚህን ጠቃሚ እድሎች በትክክል እንድትጠቀምበት ማረጋገጥ እንፈልጋለን።

የእኛ እይታ በኤሲፒኤስ እያንዳንዱ የእኛ ተማሪ ውጤታማ ሁኖ ማየት ነው እና አንተም አቅምህ በሚፈቅደው ደረጃ መድረስህን ማረጋገጥ ነው። የእኛ ዓላማ ሰፊ እድል እንዲኖር ማድረግ ነው - ጠንካራ የአካዳሚ ፕሮግራም ፣ በኮሌጅ ደረጃ ያለ ኮርስ፣ የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት (CTE) ፕሮግራም እና ኮሌጅ ዝግጁ የሚያደርግ ፕሮግራሞች። በዚህ የትምህርት ፕሮግራም የተካተቱ ሰፊ የኮርሶች ምርጫ እድል የተለያየ መንገድ በመክፈት አንተን በኮሌጅ፣ የስራ ወይም የሕይወት ውጤታማነት ላይ እንድትደርስ ማድረግ ነው።

ስኬት በራስ ጥረት ብቻ የሚሆን አይደለም፣ ነገር ግን የእኛ አስተማሪዋች፣ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዋች በኤሲፒኤስ የትምህርት ቆይታ ወቅት አንተን ለመደገፍ ተዘጋጅተው ይገኛሉ። በተጨማሪም ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ በአሰልጣኞች(ሜንተርስ) እና የንግድ መሪዋች አማካኝነት አንተ ውጤታማ እንድትሆን የሚያስፈግልህን ልምድ እንድታገኝ ድጋፍ እንዲያደርጉ እናበረታታለን። የኮሌጅ እና የስራ ማእከል ሰራተኞችን እና የትምህርት ቤት አማካሪ ድጋፍ በትክክል ተጠቀም እና በሕይወትህ በቀጣይ ለመውሰድ የምትፈልገውን እርምጃ ስታስብ የሚያስፈልህን ምክርና እና ድጋፍ ለማግኘት ጥረት አድርግ።

ዓለማችን እየተቀየረች ናት እና በመሆኑም የወደፊት ሙያ የስራ እንደዚሁ። አንተንና ተማሪዎቻችን ለዚህ ማዘጋጀት ይኖርብናል። የመጪው ትውልድ ለበርካታ ጊዜ ሙያ መቀየሩ አይቀርም ራሳቸውን እንደገና በስራው ዓለም በመፍጠር እና የተለያዪ አማራጮችን ማየት ይፈልጋሉ። ይህን ጊዜ የተለያዪ አማራጮችን ለማየት ተጠቀም የራስህን ጥንካሬ እና ፍላጎትህን ስሜትህን በማሳደግ እድሉን ተጠቀምበት። ከሁሉም በላይ በኤሲፒኤስ ያለህን ጊዜ ተደሰትበት። በአንተ ላይ እምነት አለን እና ይህ የትምህርት ልምድ አንተን ለትምህርት እንዲያዘጋጅ እንፈልጋለን።


ዶ/ር ግሪጎሪ ሲ. ሐትቺንግስ፣ ጁኒየር
የትምህርት ቤቶች ሱፕር ኢንቴንደንት(ዋና ሥራ አስኪያጅ)
የአሌክሳንደሪያ ከተማ የሕዝብ ት/ቤቶች